የቱርክ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሶሪያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።
ቱርክ ከሶሪያ ለሚደርስባት የፀጥታ ስጋት ምላሽ እንደምትሰጥ ቃል ገብታለች።
አርብ ዕለት ካደረገው ወርሃዊ ስብሰባ በኋላ የቱርክ ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት በሶሪያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መወያየቱን እና በቱርክ-ሶሪያ ድንበር ላይ እርምጃዎችን መገምገሙን ገልጿል።
"አለም አቀፍ ህግን መሰረት በማድረግ ለህዝባችን እና ለሀገራዊ ደህንነታችን ውጤታማ ጥበቃ አስፈላጊ የሆኑትን ሁሉንም እርምጃዎች ለመውሰድ እና ተግባራዊ ለማድረግ ያለን ቁርጠኝነት በድጋሚ ተነግሯል" ሲል ምክር ቤቱ በጽሁፍ ገልጿል።
ምክር ቤቱ በቱርክ የሽብር ጥቃቶች፣ በኢራቅ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እንዲሁም በሊቢያ እና ግብፅ እየተካሄደ ባለው የፖለቲካ ለውጥ ላይም መክሯል።
(አናቶሊያ የዜና ወኪል)



